በሉቃስ ወንጌል 6:45 ‘’ከልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራል‘’ ይላል ልጆችህ የሚአደርጉትና
የሚናገሩት ከልባቸው ሞልቶ የተረፈውን ነው።
‘’ወላጅ እንደረኛ‘’ ወላጆች በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ልጆቻቸው እንዴት ለልባቸው
እንደሚናገሩ ልዩ መረዳትን በመስጠት ልጆችን በህይወት ጎዳና መምራት እንደሚቻላቸው የሚረዳ
መጽሐፍ ነው።
ጸሐፊው ቴድ ትሪፕ የእግዚአብሄርን መንገድ የሚአውቅ፤ ወላጆችን የሚገነዘብ የልጆችን ባህርይ
በሚገባ የተረዳ በመሆኑ ለማን ምን እንዴት? መናገር እንዳለበት ለሰላሳ ዓመታት በመጋቢነት፤ ትምህርት
ቤት አስተዳዳሪነት ፤አማካሪነትና ይህን መጽሐፍ በዓለም ዙርያ በማስተማር ብዙ ጥበብን ያካበተ የልጆ
አባት ነው።
“ማስተዋልን የተሞላው ይህ መጽሐፍ ለልጆችህ እንዴት መናገር ስለምን መናገር ተቀዳሚውና
ግቡ [አላማው] ምን? መሆን እንዳለበትና በተግባር እንዴት እንደሚተረጎም በማስተማር እይታህን
በማስፋት የተለየ ወላጅ ያደርግሀል’’
Dr. David Powlison, Westminster Theological Seminary
ዶክተር ዳቪድ ፓውልሰን የዌስት ሚንስተር ት.ሰሚነሪ
ISBN: 978-965-7454-42-8
חוות דעת
אין עדיין חוות דעת.